ተቋሙ የ2017 ዓ.ም የመጀመሪያው ግማሽ ዓመት የሥራ አፈፃፀም ግምገማ መድረክን በኒው ሌቭል ሆቴል አካሂዷል።
በብድርና ቁጠባ አገልግሎቱ በርካቶችን ተደራሽ በማድረግ ውጥናቸው ከግብ እንዲደርስ፣ህልማቸው ዕውን እንዲሆን የፋይናንስ አካታችነቱን በማጠናከር አይነተኛ ሚና እየተጫወተ ይገኛል። የወጣቶችና ሴቶችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሳደገ በድሬዳዋ አስተዳደር በከተማም በገጠርም ሻገር ብሎም በሐረርና ጅግጅጋ አድማሱን ማስፋት ችሏል። ድሬ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም።
ድሬ ማይክሮ ፋይናንስ የሥራ አፈፃፀም የግምገማ መድረኩን ያካሄደ ሲሆን የ2017 ዓ.ም የመጀመሪያው ግማሽ ዓመት የተቋሙ የተጠቃለለ የብድርና ቁጠባ ዕቅድ አፈፃፀም ሲቀርብ በግማሽ ዓመቱ ከ410 ሚሊየን ብር በላይ ተቋሙ ለደንበኞቹ ማሰራጨት መቻሉ በሪፖርቱ ተመላክቷል።
ለጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችም ከ395 ሚሊየን ብር በላይ ብድር በግማሽ ዓመቱ መሥጠት የተቻለ ሲሆን ከ183 ሚሊየን ብር በላይ ብድር በማስመለስም ውጤታማ አፈፃፀም መመዝገቡ የተጠቆመ ሲሆን የቁጠባ አሰባሰብን በማሳደግ፣የሴቶችንና የወጣቶችን ተጠቃሚነትን ከማጎልበት አንፃርም ከፍተኛ ዕመርታ መታየቱም ተገልጿል።
ተቋሙ ትርፋማነቱን ለማሳደግ በሠራቸው መጠነ-ሰፊ ስራዎች በግማሽ ዓመቱ ከ60 ሚሊየን ብር በላይ ትርፍ ያስመዘገበ ሲሆን ይህን ትርፋማነቱን ለማስቀጠል የሚሰጣቸውን የብድርና ቁጠባ አገልግሎቶችን የማሳደግና የማዘመን ሥራዎችም በቀጣይ በስፋት እንደሚሰሩም ተጠቁሟል።
በ2017 ዓ.ም በመጀመሪያው ግማሽ ዓመት ድሬ ማይክሮ ፋይናንስ በተቋሙ የብድር ደንበኞች ላይ ያለው ጠቅላላ የብድር መጠንም ከ1.2 ቢሊየን ብር በላይ መድረሱም ተገልጿል።
በሪፖርት ግምገማ መድረኩ ላይም የድሬ ማይክሮ ፋይናንስ የቅርንጫፎች፣ የተጠቃለለ የኦፕሬሽንና የፋይናንስ ሥራ ክፍል የሥራ አፈፃፀም ሪፖርቶችም ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል።
በግምገማው መድረክ ማጠቃለያ ላይ የድሬ ማይክሮ ፋይናንስ ዋናስራአስፈፃሚ አቶ ተሾመ አበበ የብድር ጥራት አጠባበቅ የሚሰጡ ብድሮች ውጤታማ እንዲሆኑና የብድር አመላለስ ስጋትን ከመቅረፍ አንጻር ቁልፍ ሚና ስላለው የብድር ጥራት አጠባበቅ ላይ ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት በአፅንኦት መሥራት እንደሚገባ አሳስበዋል።
የዲጂታል ቁጠባን ማሻሻል፣ በታማኝነት ደንበኞችን ማገልገል፣ውዝፍ ብድርን በቁርጠኝነትና በከፍተኛ ተነሳሽነት ማስመለስ አቶ ተሾመ አበበ አቅጣጫ የሰጡባቸው ሌሎች አንኳር ጉዳዮች ናቸው።





Leave a Reply