ድሬ ማይክሮ ፋይናንስ 19ኛ መደበኛ እና 4ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤውን አካሄደ
ድሬ ማይክሮ ፋይናንስ አክሲዮን ማኅበር የባለአክሲዮኖች 19ኛ መደበኛ እና 4ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤውን በድሬዳዋ ኒው ሌቭል ሆቴል አካሄደ
በተካሄደው በ19ኛው መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ጉባኤው በአራት አጀንዳዎች ላይ ማለትም እ.ኤ.አ የ2023/24 የሒሳብ ዓመት የዳይሬክተሮች ቦርድ ዓመታዊ ሪፖርት እና እ.ኤ.አ የ2023/24 የሒሳብ ዓመት የውጭ ኦዲተር ዓመታዊ ሪፖርትን በማድመጥ ተወያይቶ በሙሉ ድምፅ ያፀደቀ ሲሆን በውጭ ኦዲተር የማኅበሩ የሒሳብ ሪፖርት በቀረበበት ወቅት የአክሲዮን ማኅበሩ የሒሳብ ሪፖርት ደረጃውን በጠበቀ፣ ጥልቅና ሙያዊ በሆነ አኳኋን በዓለም አቀፍ የፋይናንስ ሪፖርት መሠረት መዘጋጀቱም ተገልጿል፡፡
ጉባኤው የአክሲዮን ዝውውር ጉዳይ ላይ እንዲሁም የተጠራቀመ የማኅበሩ የተጣራ ትርፍ አደላደልና አከፋፈል ላይም ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል፡፡
ጠቅላላ ጉባኤው 4ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤውንም ያካሄደ ሲሆን የአክሲዮን ማኅበሩ መመስረቻ ፅሁፍ ማሻሻያ ላይ ተወያይቶ ማሻሻያውን በሙሉ ድምፅ አፅድቋል፡፡
ከተያዘው አጀንዳ አንዱ የአክሲዮን ማኅበሩን ካፒታል ማሳደግ ሲሆን አሁን ካለው የአክሲዮን ማኅበሩ ዕድገትና ወደፊትም ተቋሙን ይበልጥ በፋይናንስ ዘርፉ ዕድገቱን በአስተማማኝ ሁኔታ ከማስቀጠል አንጻር ካፒታሉን ማሳደግ በማስፈለጉ በ19ኛው መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ በተወሰነው መሠረት በተጠራቀመው የትርፍ አደላደል ውሳኔ መሠረት 350 ሚሊየን ብር የነበረው የተከፈለ ካፒታል ወደ 500 ሚሊየን ብር እንዲያድግ ውሳኔ አሳልፏል፡፡












Leave a Reply