ወጣት ሰኢድ ዘይኑ
የድሬ ማይክሮ ፋይናንስ የዎሽ ብድር አገልግሎት ተጠቃሚ
ወጣት ሰኢድ ዘይኑ ድሬ ማይክሮ ፋይናንስ ከአኳ ፎር ኦል ጋር በቅንጅት ባመቻቸው የዎሽ ብድር አገልግሎት ተጠቃሚ የሆነ ወጣት ስራ ፈጣሪ ነው፡፡ በንጽህና መጠበቂያ ምርቶች ላይ ማለትም ፈሳሽ ሳሙና፣ሻምቦ፣በረኪናና ተያያዥ ምርቶችን ማምረት ላይ የተሰማራው የዎሽ ብድር አገልግሎቱ ተጠቃሚ ደንበኛ ለምርቶቹ ማጓጓዣ የሚሆን የተሽከርካሪ ብድር አገልግሎት ከድሬ ማይክሮ ፋይናንስ ማግኘት ችሏል፡፡
በዚህም በፊት ላይ በተሸከርካሪ ዕጦት ምርቶቹን ደንበኞቹ ጋር ተዘዋውሮ ለማሰራጨት ይቸገር የነበረ ሲሆን አሁን ላይ ግን ምርቶቹን የሚያጓጉዝበት የተሽከርካሪ ችግሩ በመፈታቱ ከድሬዳዋ ባሻገርም ወደ አጎራባች አካባቢዎች ጭምር ምርቶቹን ተደራሽ ሆነዋል፡፡ የድሬ ማይክሮ ፋይናንስ የንጹህ መጠጥ ውሃ፣ሳኒቴሽንና ሃይጅን የብድር አገልግሎት ለስራው ተደራሽነት በእጅጉ እንደጠቀመውም ነው ወጣት ሰኢድ ዘይኑ የተናገረው፡፡
ዘማስ፣ቀፊራና ሸጋ በሚሉ የብራንድ መለያዎች ምርቶቹን እያመረተ ያለው ወጣት ዘይኑ ሰኢድ ከ30 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ ዕድል መፍጠር ችሏል፡፡ ያነጋገርናቸውም በድርጅቱ የስራ ዕድል የተፈጠረላቸው ሰራተኞች በፊት ስራ ያልነበራቸው ሲሆን ድርጅቱ ባመቻቸላቸው የስራ ዕድል ተጠቃሚ መሆን በመቻላቸው እራሳቸውንና ቤተሰባቸውን ማስተዳደር እንደቻሉና የሙያ ክህሎትም ማግኘት መቻላቸውን ገልጸውልናል፡፡
ወጣት ዘይኑ ድሬ ማይክሮ ፋይናንስ እየሰጠው ያለው የዎሽ የብድር አገልግሎት ማህበረሰቡን በእጅጉ ተጠቃሚ የሚያደርግ መሆኑን ይናገራል፡፡ ለዚህም እራሱን አብነት አድርጎ በመጥቀስ ማኅበረሰቡ በዎሽ የብድር አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆን መልዕክቱን አስተላልፏል፡፤






Leave a Reply