ድሬማይክሮፋይናንስበአዲስአበባቦሌሚካኤልአካባቢአዲስቅርንጫፋንበይፋአስመረቀ

ድሬ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም በመዲናችን አዲስ አበባ ቦሌ ሚካኤል አካባቢ አዲስ ቅርንጫፋን በይፋ አስመርቆ ሥራ ጀመረ።

ተቋሙ አዲሱን ቅርንጫፍ መክፈቱ የፋይናንስ ተደራሽነትና አካታችነትን ለማስፋት የሚያግዝ እርምጃ መሆኑ በመክፈቻ ሥነ-ስርዓቱ ላይ ተገልጿል።

በምረቃ ሥነ-ስርዓቱ ላይ የድሬ ማይክሮ ፋይናንስ ዋና ስራአስፈፃሚ አቶ ተሾመ አበበ እንደገለፁት ድሬ ማይክሮ ፋይናንስ ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ ለማኅበረሰብ የተመሰረተ እና ተደራሽ የፋይናንስ አገልግሎት መስጠትን ዋነኛ ተልዕኮው አድርጎ እየሰራ መሆኑን ጠቅሰው በአሁኑ ወቅት በተቋሙ በደንበኞች እጅ ያለ የብድር መጠን /Total Loan Outstanding/  ከ1.7 ቢሊዮን ብር በላይ መድረሱን እና ከ111 ሺህ በላይ የብድርና ቁጠባ ደንበኞችን እያገለገለ መሆኑን ገልጸዋል።

ድሬ ማይክሮ ፋይናንስ በተለያዩ የክልል ከተሞች ቅርንጫፎችን በመክፈት እየሰራ መሆኑን የጠቀሱት አቶ ተሾመ አዲሱ የቦሌ ሚካኤል ቅርንጫፍ በአዲስ አበባ የመጀመሪያው የተቋሙ ቅርንጫፍ መሆኑንም ተናግረዋል።

ተቋሙ ከመደበኛ የብድርና ቁጠባ አገልግሎት በተጨማሪ ወለድ አልባ አገልግሎቶች፣ የማሽነሪ ሊዝ ብድር እና ከታዳሽ  ኃይል ጋር የተያያዙ አዳዲስ የፋይናንስ አማራጮችን እያቀረበ ወደ ህብረተሰብ እየቀረበ መሆኑን አቶ ተሾመ ጨምረው ገልጸዋል ።

በምርቃት መርሃግብሩ ላይ የተገኙት ተጋባዥ ዕንግዶች ድሬ ማይክሮ ፋይናንስ በአዲስ አበባ ቦሌ ሚካኤል ቅርንጫፍ መክፈቱ እንዳስደሰታቸው ገልጸው የቅርንጫፉ መከፈት ተደራሽነቱን በይበልጥ በማስፋት ኅብረተሰቡን በቅርበት ለማገልገል አስተዋፅኦው ከፍተኛ መሆኑን ገልፀዋል።

በመክፈቻ ስነ-ስርዓቱ ላይ የመንግሥትና የተቋማት ኃላፊዎች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች፣ የተቋሙ አመራሮችና ሰራተኞች ተገኝተዋል።

admin Avatar

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *