የቁጠባ መሠረት ማስፋት ላይ ትኩረት ሰጥቶ መሥራት እንደሚገባ ተገለፀ፡፡
ድሬ ማይክሮ ፋይናንስ የ2018 የመጀመሪያው ግማሽ ዓመት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት የግምገማ መድረክ በሐረር ከተማ ለሁለት ቀናት ተካሂዷል፡፡
በውይይት መድረኩ በድሬ ማይክሮ ፋይናንስ የሚገኙ ቅርንጫፎች የ2018 የመጀመሪያው ግማሽ ዓመት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርታቸውን ያቀረቡ ሲሆን የኦፕሬሽን እና የፋይናንስ የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡
በውይይት መድረኩ ላይ በመጀመሪያው ግማሽ ዓመት ለ2,115 የብድር ደንበኞች ብድር ለማሰራጨት ታቅዶ ለ2,084 የብድር ደንበኞችን ተጠቃሚ ማድረግ የተቻለ ሲሆን በዚህም የዕቅዱን 99 በመቶ ማሳካት ተችሏል ፤ በግማሽ ዓመቱ 560,559,095 ብር ለማበደር ታቅዶ 511,881,132 ብር ማበደር የተቻለ ሲሆን የዕቅዱን 91 በመቶ ማሳካት መቻሉ በውይይት መድረኩ ተገልጿል፡፡
በቁጠባ አሰባሰብ ረገድም በግማሽ ዓመቱ የዕቅዱን 119 በመቶ መፈጸም ተችሏል፤ ሴቶችን እና ወጣቶችን ተጠቃሚ ለማድረግ በተሰራ ስራ በግማሽ ዓመቱ ለ1,231 ሴቶች ብር 320,641,086 ለማበደር ታቅዶ ለ1,022 ሴቶች የዕቅዱን 83 በመቶ ፣ በብር ደግሞ 283,971,200 የዕቅዱን 89በመቶ ማሳካት ተችሏል፤ ወጣቶችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በመጀመሪያው ግማሽ ዓመት በአጠቃላይ ከሚሰጠው ብድር ውስጥ ለ821 ወጣቶች ብር 213,760,724 ለማበደር ታቅዶ ለ1,282 ወጣቶች የዕቅዱን 156 በመቶ ወጣቶች ፣ በብር ደግሞ 357,377,503 ብር በማሰራጨት የዕቅዱን 167 በመቶ ማበደር መቻሉ ተመላክቷል፡፡
የተጠቃለለ በብድር አመላለስ ረገድም የዕቅዱን 98 በመቶ ማሳካት የተቻለ ሲሆን ፣ የዘመን ብድር አመላለስ ላይም የታየው ለውጥ አበረታች መሆኑን በመጥቀስ የውዝፍ አመላለስ ላይ ከበፊቱ በላቀ ሁኔታ ትኩረት በመሥጠት መስራት እንደሚጠበቅም በዋና ስራ አስፈጻሚው አቶ ተሾመ አበበ ተመላክቷል፡፡
ዋና ሥራ አስፈጻሚው የቁጠባ አሰባሰብ ላይ ዕመርታ እየታየ መሆኑን በመጥቀስ በይበልጥ የቁጠባ መሠረትን ማስፋት ላይ በቁርጠኝነት፣ በተቀናጀና በተናበበ መልኩ መሥራት እንደሚገባ አፅንኦት ሰጥተዋል፡፡
የደንበኞች ዕርካታን በማሻሻልና በማሳደግ ረገድ እየተሰሩ ያሉ ሥራዎች የደንበኛን ዕርካታን በሚጨምሩ አግባቦች መቃኘት እንዳለበትና የደንበኞች ዕርካታ የተቋማቸው ዋነኛ ማጠንጠኛ መሆኑን በመግለፅ በቀጣይ የደንበኞች ዕርካታ ላይ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ሁኔታ አፅንኦት ተሰጥቶ እንደሚሰራበት ገልፀዋል፡፡
በገጠር ወረዳዎች ላይ ያሉ የኅብረተሰብ ክፍሎችን የብድርና ቁጠባ ተደራሽነት ማስፋት፣የሴቶችና ወጣቶችን ተጠቃሚነት በይበልጥ ማጎልበት በቀጣይ የተቋሙ ዋና የትኩረት መስኮች መሆናቸውም ተነስቷል፡፡










Leave a Reply