ገነት ብርሃኑ የድሬ ማይክሮ ፋይናንስ ከዚራ ቅርንጫፍ የመደበኛ ብድርና ቁጠባ አገልግሎት ደንበኛ
ድሬ ማይክሮ ፋይናንስ የሴቶችን የፋይናንስ ተጠቓሚነት ማሳደግና በምጣኔ ሀብታዊ እንቅስቃሴ ውስጥ አይነተኛ ሚና እንዲጫወቱ ማድረግ ዋነኛ የትኩረት ማዕከሉ ነው፡፡ በዚህም በርካታ ሴቶች ከማጀት ወደአደባባይ በማውጣት ግንባር ቀደም የዕድገትና የልማት ተዋንያን እንዲሆኑ አስችሏል፡፡ ለዚህ ደግሞ አብነት ከሚሆኑት መካከል ወጣት ገነት ብርሃኑ ተጠቃሽ ናት፡፡ ከድሬ ማይክሮ ፋይናንስ ጋር ከ10 ዓመት የዘለቀ የደንበኝነት ታሪክ ያላት ሲሆን ከ50ሺ ብር የጀመረው የብድር አገልግሎት ተጠቃሚነቷ አሁን ላይ 2.5 ሚሊየን ብር የብድር አገልግሎት ተጠቃሚነት ላይ የደረሰች ሲሆን በዚህም በስራ እንዲሁም በቤተሰብ ህይወቷ ላይ ብዙ ለውጦችን ማየት ችላለች፡፡ በምግብ እና በባልትና ስራዎች ላይ የተሰማራችው ገነት ብድሯን በአግባቡ ለታለመለት ዓላማ በማዋል ብሎም በተገቢው ሁኔታ ብድሯን በመክፈል ምስጉን ደንበኛ ናት፡፡ ድሬ ማይክሮ ፋይናንስ ያደረገላት የፋይናንስ ድጋፍ ለስራዋ ውጤታማነት ትልቅ መሠረት የጣለ መሆኑን የምትገልፀው አብነቷ ደንበኛ አሁንም ከተቋሙ ጋር ያላትን አጋርነት በማጠናከር በቀጣይ ደረጃውን የጠበቀ ትልቅ ካፌ ባለቤት መሆንን ታልማለች፡፡ የመስራት ሃሳብ እና ፍላጎት ኖሯቸው የፋይናንስ ዕጥረት ለገጠማቸው ሰዎች ድሬ ማይክሮ ፋይናንስ አለኝታ የሆነ ተቋም ነውና ተቋሙን በመቅረብ ተጠቃሚ ሁኑ የሚለው መልዕክቷ ነው፡፡






Leave a Reply