“ድሬ ማይክሮ ፋይናንስን እንደ ቤተሰቤ ነው የምቆጥረው”
ሰርካለም ሲሳይ
የድሬ ማይክሮ ፋይናንስ ሳቢያን ቅርንጫፍ ደንበኛ
ሰው ከተሰማራ እንደ የስሜቱ ፤
ከዋለበት ሜዳ አይቀርም ማፍራቱ ፡፡
አይቀርም ማፍራቱ ፡፡
ስትል በመረዋ ድምጽዋ ድምጻዊት መንበረ በየነ ሰው በተሰማራበት የስራ መስክ ትጋትን ከስራ ፍቅርና ከጽናት ጋር ከታጠቀ ውጤታማ የማይሆንበት ምንም ምክንያት እንደሌለ በጥበባዊ ስራዋ ታስገነዝበናለች፡፡
የዛሬው ዕንግዳችንም ከድሬ ማይክሮ ፋይናንስ ጋር አብሮ በመስራት ጥረትን፣ፅናትን፣ ትጋትንና የማይናወጥ የሥራ ፍቅርን ገንዘቡ አድርጎ በተለያዩ የስራ መስኮች በመሰማራት ውጤታማ መሆን የቻለ የተምሳሌቶቹ ገፅ ባለታሪካችን ነው፡፡
አቶ ሰርካለም ሲሳይ ይባላል፡፡
ትውልድና ዕድገቱ ቁልቢ ሲሆን በ1992 ዓ.ም ወደ ድሬዳዋ በመምጣት ኑሮን ለማሸነፍ፣ ከራስ አልፎም ለሌሎች ለመትረፍ ደፋ ቀና በማለት የተለያዩ ሥራዎችን ሰርቷል፡፡ ከሰራቸው ሥራዎችም መሃል በነዳጅ ማደያ ተቀጥሮ የሰራው ዕንግዳችን ለተወሰነ ጊዜ በማደያ ከሰራ በኋላ የራሱን ስራ መስራት በማሰብ ወደ ድሬ ማይክሮ ፋይናንስ መጣ፡፡ ድሬ ማይክሮ ፋይናንስም ለስራ ፍቅር ላላቸው፣ሰርተው ለመለወጥ ስንዱ ለሆኑት በሩ ክፍት ነውና በደስታ ተቀበለው፡፡ ታታሪው፣ በስራ ፍቅር ለወደቀው፣ ዛሬ ላይ ቆሞ የነገ ስኬቱ ለሚናፍቀው ዕንግዳችን ሰርካለም ሲሳይ ድሬ ማይክሮ ፋይናንስ በሩን ወለል አድርጎ ከፈተለት፡፡ እናም ለመጀመሪያ ጊዜ ከድሬ ማይክሮ ፋይናንስ ሳቢያን ቅርንጫፍ 300ሺህ ብር በመበደር የራሱን ስራ አንድ ብሎ ጀመረ፡፡
ዕንግዳችን በከብት ዕርባታ፣ በብሉኬት ማምረትና በሌሎችም የሥራ ዘርፎች በመሰማራት ለራሱም ለሌሎችም እንዲተርፍ ድሬ ማይክሮ ፋይናንስ አይነተኛ ሚና እንደተጫወተ ይገልጻል፡፡ ማንም ለስራው መነሻ የሚሆን ካፒታል በማይሰጠው ሰዓት አለሁልህ ያለው፣ ለስኬቱ እርሾ የሆነው ድሬ ማይክሮ ፋይናንስ መሆኑን በልበሙሉነት ይናገራል፡፡
አሁን ላይ ላለበት የዕድገት ደረጃ መሠረት የጣለለት ድሬ ማይክሮ ፋይናንስ መሆኑንም በማከል፡፡
አሁን ላይ 50 ላሞች ያሉት እና ለድሬዳዋ ማኅበረሰብ ወተት የሚያቀርብ፤ ከ2000 በላይ ብሉኬት በቀን በማምረት ብሎም ለኮንስትራክሽን ዘርፉም ግብዓት እየሆነ ያለው ሰርካለም ሲሳይ ከድሬ ማይክሮ ፋይናንስ ጋር አብሮ መስራት ውጤታማ ያደርጋል ይላል፡፡ ከድሬ ማይክሮ ፋይናንስ ጋር አብሮ በመስራቱ ውጤታማና ስኬታማ መሆኑን በማንሳት፡፡
ከ20 በላይ ለሚሆኑ ሰዎች የሥራ ዕድል የፈጠረው ሰርካለም ሲሳይ ድሬ ማይክሮ ፋይናንስን በአንድ ቃል ግለጽልን ስንለው ድሬ ማይክሮ ፋይናንስ እንደ ቤተሰቤ ነው የምቆጥረው ሲል ምላሹን ሰጥቶናል፡፡ ለሥራው የሚሆነው ብድር በፈለገ ሰዓት ድሬ ማይክሮ ፋይናንስ አለኝታነቱን ስላሳየው፣ እያሳየውም ስላለ እንዲሁም ለሥራ የሚሆነውን ብር በፈለገ ጊዜ ተቋሙ አስፈላጊውን ድጋፍ ስላደረገለት በዚህ ምክንያት እንዲህ እንዳለው ገልጾልናል፡፡
ወጣቶችና ሴቶችን በማገልገልና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸውን በማሳደግ አብይ ሚና እየተጫወተ መሆኑን የሚገልፀው ዕንግዳችን በተለይም ወጣቶች ከተቋሙ ጋር አብረው በመሥራትና የወሰዱትን ብድር በአግባቡ ከተጠቀሙና የሚሰሩትን ስራ በቅድሚያ አጥንተውና ለይተው ከሰሩ በኑሮአቸው ላይ ለውጥ ማምጣት፣ ለሌሎችም ለመትረፍ የማይችሉበት ምክንያት የለምና ይበደሩ! ይስሩ! በአግባቡ ብድራቸውን ይክፈሉ ማሳረጊያ መልዕክቱ ነው!





Leave a Reply