‹‹ከድሬ ማይክሮ ፋይናንስ ጋር ሆኜ አስመጪ እና አከፋፋይ ለመሆን በርትቼ እየሰራሁ ነው››

    አቶ ከድር ሙባረክ

የአበሩስ ሸቀጣ ሸቀጥ  ሱቅ ባለቤት

የድሬ ማይክሮ ፋይናንስ የተምሳሌቶች ገጽ ከድሬ ማይክሮ ፋይናንስ ጋር አብሮ በመሥራት ለራሳቸው የሥራ ዕድል ከመፍጠር ባለፈ ለሌሎችም እየተረፉ ያሉ ተምሳሌት ሥራ ፈጣሪዎችን ማስቃኘቱን እንደቀጠለ ነው፡፡

በዚህ ጥንቅር ከድሬ ማይክሮ ፋይናንስ መስቀለኛ ቅርንጫፍ ደንበኞች አንዱ የሆኑትንና በሸቀጣሸቀጥ ንግድ የተሰማሩትን አቶ ከድር ሙባረክን በዕንግድነት ይዘንላችሁ ቀርበናል፡፡  

ወደ ሸቀጣ ሸቀጥ ሱቁ የመጣውን ደንበኛ በደስታ እየተቀበለ ሲያስተናግድ ያገኘነው  አቶ ከድር ሙባረክ ሸቀጣ ሸቀጥ  መደብሬን  ሙሉ አድርጎ ደስተኛ ያደረገኝ፤ ሳቄን ሙሉ ያደረገው ድሬ ማይክሮ ፋይናንስ ነው  ሲል ገና ከበር ስንገባ  በደስታ ተውጦ ተቀበለን፡፡

የድሬ ማይክሮ ፋይናንስ ሰራተኞች ሸቀጣ ሸቀጥ ሱቄ  መጥተው ስለ ተቋሙ አገልግሎት ሲነግሩኝ ይሄ ቤቴ ድረስ የመጣውን ዕድል እንዲያመልጠኝ አልፈለኩም ያለው አቶ ከድር ወዲያው በወለድ አልባ የፋይናንስ አገልግሎት ለሱቄ የሚሆን ዕቃ እንዲገዛልኝ ስጠይቅ በአካባቢዬ የሚገኘው የድሬ ማይክሮ ፋይናንስ መስቀለኛ ቅርንጫፍ በጥሩ ሁኔታ አስተናግዶ የምፈልገውን ዕቃ በአጭር ጊዜ አስረከበኝ ይሄ ለኔ የሁሉ ነገር መጀመሪያ ነበር ይላል አቶ ከድር ሙባረክ ፡፡

ዛሬ እንዲህ ሱቄ ሙሉ የሆነው በድሬ ማይክሮ ፋይናንስ ነው ያለው አቶ ከድር ስራ ለሚሰራ ሰው ድሬ ማይክሮ ፋይናንስ አቻ የሌለው የደኃ እናት የሆነ ተቋም መሆኑን ይመሰክራል፡፡

ብዙዎች ከተቋሙ ተበድረው ሲለወጡ አይቻለሁ የሚለው አቶ ከድር እኔም ይሄንን ዕድል በመጠቀም ስራዬን በብቃት እየተወጣሁ ነው ይላል፡፡

ድሬ ማይክሮ ፋይናንስ ለትርፍ ብቻ የተቋቋመ ተቋም አይደለም እንደ እኔ ላሉ በርካቶች  የሥራ ዕድል እንዲፈጥሩ ለሌሎችም እንዲተርፉ አይነተኛ ሚና መጫወቱን አቶ ከድር ሙባረክ  ይገልፃል። ብድርን ለተፈለገው ዓላማ ማዋል ከተቻለ ማደግ፣መለወጥ የሚያስችል ነውና ኅብረተሰቡ በተለይም ወጣቶች ተበድረው እንዲሰሩ፣ በአግባቡም ብድራቸውን እንዲከፍሉ አበረታታለሁ  ይላል የድሬ ማይክሮ ፋይናንስ መስቀለኛ ቅርንጫፍ ደንበኛ አቶ ከድር ሙባረክ።

የኔን ሱቅ እንደሞላልኝ ሳቄን እንዳሳመረው ሌሎችም ይሄንን እንዲጠቀሙ እጋብዛለሁ የሚለው አቶ ከድር ቀጣይ ዕቅዴ ከዱባይ፤ከቱርክ፤ከቻይና የተለያዩ ዕቃዎችን በማምጣት በተመጣጣኝ ዋጋ ምርቶችን እና ሸቀጣሸቀጦችን ማከፋፈል ነው የሚለው ተምሳሌቱ ሥራ ፈጣሪ ከድር ሙባረክ ድሬ ማይክሮ ፋይናንስ አጋሬ ነው እና ከድሬ ማይክሮ ፋይናንስ ጋር ይሄ እንደሚሳካ ሙሉ ዕምነት አለኝ ይላል፡፡

 በፈገግታ እንደተቀበለን በፈገግታው የሸኘን አቶ ከድር ከሱቁ እየወጣን አንድ መልዕክት ነገረን የደሃ መድኃኒት ለሆነው ለድሬ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም ምስጋና  አቅርቡልኝ አለ እኛም ተቀበልን ‹‹የድሃ መድኃኒት ድሬ ማይክሮ ፋይናንስ›› 

“I am working hard to become an importer and distributor with Dire Micro-Finance”

admin Avatar

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *