“ካልቆጠብኩቅርቅርይለኛል”

ሰለሞን ተፈራ

የድሬ ማይክሮ ፋይናንስ ፖሊስ መሬት ቅርንጫፍ የመደበኛ ብድርና ቁጠባ አገልግሎት ደንበኛ


አቶ ሰለሞን ተፈራ የድሬ ማይክሮ ፋይናንስ ፖሊስ መሬት ቅርንጫፍ የመደበኛ ብድርና ቁጠባ አገልግሎት ደንበኛ ሲሆኑ በንፅህና መስጫ አገልግሎት /በሻወር ቤትና መፀዳጃ ቤት/ አገልግሎት የተሰማሩ ምስጉን ደንበኛ ናቸው፡፡


ለሥራቸው መነሻ የሆናቸውና ምቹ መደላድል የፈጠረላቸው ድሬ ማይክሮ ፋይናንስ ያመቻቸላቸው የፋይናንስ ድጋፍ ነው፡፡ ስራቸውን ሲጀምሩ በ4 ሻወር ቤትና በ2 መፀዳጃ ቤቶች ሲሆን አሁን ላይ የሻወር ቤታቸው ወደ 10፣የመፀዳጃ ቤቶቹ ደግሞ ወደ 5 በማሳደግ ለአሸዋና አካባቢው ማኅበረሰብ ከፍተኛ አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ፡፡


ቁጠባ ለአቶ ሰለሞን የህይወቱ መሠረት ፣የህይወቱም መርህ ነው፡፡ ያለቁጠባ መኖር ለእሱ ከባዱ ነገር ነው፡፡ ቁጠባ ለእኔ ሱስ ነው ካልቆጠብኩ እራሱ ቅር ቅር ይለኛል ይላል ቁጠባን ባህል አድርጎ ያሰረፀው ዕንግዳችን፡፡ በመቆጠቡ በህይወቱ፣ በስራው ያገኘውን ጥቅም ያውቀዋልና ቁጠባን የህይወቱ አንድ አካል አድርጎ ይዞታል፡፡ ሌሎችም ይህን ባህል ቢያዳብሩ በእጅጉ እንደሚጠቀሙም ከልምዱ ያጋራል፡፡


በድሬ ማይክሮ ፋይናንስ ከፍተኛ ዕገዛ እንደተደረገለትና በተቋሙ አገልግሎት ደስተኛ መሆኑን የሚገልፀው አቶ ሰለሞን ተፈራ ለተቋሙ ድጋፍና አለኝታነት ምስጋናውን በማቅረብ ከሌሎች የፋይናንስ ተቋማት ፈጥኖ ደራሽና የማኅበረሰቡ አለኝታ ድሬ ማይክሮ ፋይናንስ ነው ሲልም የድሬ ማይክሮ ፋይናንስን አበርክቶ በጉልህ ይጠቅሳል፡፡
በቀጣይም ከድሬ ማይክሮ ፋይናንስ ጋር ያለውን ቤተሰባዊ እና የደንበኝነት ግንኙነት በማጠናከር ስራውን ለማስፋፋት ያልማል ምስጉን ደንበኛ አቶ ሰለሞን ተፈራ፡፡ እኛም ያሰብከው ይሳካ፣ ስራህ ፍሬያማህ ይሁንልህ እያልን እንደ መርሃችን አንተንም ሌሎች ደንበኞቻችንን በፍቅር ማገልገላችንን አጠናክረን እናስቀጥላለን፡፡

በፍቅር እናገለግሎታለን!

admin Avatar

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *