ድሬ ማይክሮ ፋይናንስ በማህበራዊ ትስስር ገጾቹ ለደንበኞቹና ለድሬዳዋ ማኅበረሰብ ተደራሽነቱን ለማስፋት እየሰራ ይገኛል፡፡ በተለይም በፌስቡክ ገጹ በአዲስ መልክ የተለያዩ ስራዎችን እየሰራ ነው፡፡
‹‹ተምሳሌቶቹ›› በሚል ጥንቅር ውጤታማ የድሬ ማይክሮ ፋይናንስ ደንበኞች የሕይወት ተሞክሮ በተከታታይ ጥንቅሮች የሚቀርብ ሲሆን ለዛሬ የመጀመሪያ ዕንግዳ ያደረግነውን የድሬ ማይክሮ ፋይናንስ ደንበኛ ከድሬ ማይክሮ ፋይናንስ ጋር ስላለው ደንበኝነትና በተያያዥ ጉዳዮች ላይ ያደረግነውን ቆይታ ይዘንላችሁ ቀርበናል፡፡
‹‹ ድሬ ማይክሮ ፋይናንስ የችግሬ ደራሽ ነው››
ወጣት ወንድማገኝ ተሬሳ
የድሬ ማይክሮ ፋይናንስ የረዥም ጊዜ ደንበኛ
ወንድማገኝ ተሬሳ በተለያዩ የንግድ ስራዎች ላይ የተሰማራ የድሬ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም የረጅም ጊዜ ደንበኛ ነው፡፡ ይህ የተቋሙ ደንበኛ ከድሬ ማይክሮ ፋይናንስ ጋር የጠበቀ ቁርኝት አለው፡፡ ድሬ ማይክሮ ፋይናንስ በስራዎቹ ውስጥ ሁሉ አጋርነቱን ያሳየው ተቋም መሆኑን ምስክርነቱን ይህ የተቋሙ የረጅም ጊዜ ደንበኛ ምስክርነቱን ይሰጣል፡፡
ወንድማገኝ እንደሚለው ከአራት ዓመት በፊት እሱና ቤተሰቡ በንግድ ስራ ላይ ለመሰማራት ፈልገው በእጃቸው ምንም ገንዘብ አልነበረም፡፡ እንዴት አድርገን ይህን ችግር መቅረፍ እንችላለን ብለው ሲጨነቁ ድሬ ማይክሮ ፋይናንስ አለኝታነቱን አሳያቸው፡፡ እናም ከማይክሮ ፋይናንስ በወሰዱት ብድር በትንሽ የጀመሩት የንግድ ሥራ ዛሬ ላይ ሰፍቶ ሲመለከተው ደስታው ወደር የለውም፡፡
ከቤተሰቦቹ ጋር በጋራ በመሆን ለግሮሰሪ ስራ ብድር ወስደው ወደስራ መግባቱን የሚናገረው ወንድማገኝ ከቤተሰቦቼ አልፎ በአሁኑ ወቅት የራሴን የንግድ ስራ እየሰራሁ በህይወቴ ብዙ ለውጥ አምጥቻለሁ በማለት መነሻውን ይገልፃል፡፡
ድሬ ማይክሮ ፋይናንስ የቤተሰቤን ያህል የምወደው ተቋም ነው ምክንያቱም የኔንም ሆነ የቤተሰቤን ህይወት የለወጠ፣ ካለንበት ችግር አውጥቶ በጥሩ የህይወት መስመር ያስገባን በመሆኑ ሁሌም አመሰግነዋለሁ የሚለው ወጣት ወንድማገኝ ቸገረኝ ብለህ ብድር የሚሰጥ ወዳጅ ዘመድ በሌለበት ድሬ ማይክሮ ፋይናንስ ደራሽነቱን ያረጋገጠ የድሬ አለኝታ መሆኑን በኩራት ይናገራል፡፡
ቆጥቡ ፤ተበደሩ፤ በጊዜ ክፈሉ የሚለው ወጣት ወንድማገኝ ብድር ጥሩ አይደለም የሚሉ አካላት ሰው በብድር ሰርቶ እራሱን፣ቤተሰቡንም ከመቀየር ባለፈ የስራ ዕድልም በመፍጠር ለብዙኃን እንዲተርፍ የሚያስችል በመሆኑ ሰዎች ብድር ተበድሮ መስራትን መፍራት የለባቸውም በማለት ከህይወት ተሞክሮው ያካፍላል፡፡
ድሬ ማይክሮ ፋይናንስ ተበድረው ለሚሰሩ ሰዎች ሁሌም በሩ ክፍት ነውና ተቋሙን ቀርበው አብረው በጋራ መስራት ይቻሉ የሚለው ወንድማገኝ እኔን ከባዶ ያነሳኝ ተቋምን መጥተው ሁሉም ይዩት ሲል መልዕክቱን ያስተላልፋል፡፡
“ከምንም ተነስቼ የባጃጅ ባለቤት ያደረገኝ፤ የራሴን የውሃ ማከፋፈያ እንድከፍት የረዳኝ ድሬ ማይክሮ ፋይናንስ ነው፡፡ የድሬ ማይክሮ ፋይናንስ አመራሮችና ሰራተኞችም እንደወንድም እየመከሩኝ፣ እንደዘመድ እያዋዩኝ ችግሬን የተሻገርኩት በድሬ ማይክሮፋይናንስ ተቋም እና ሁሌም ደከመኝ በማያውቁት የተቋሙ ሰራተኞችን በመሆኑ ሁሉንም አመሰግናለሁ” ብሏል፡፡
ድሬ ማይክሮ ፋይናንስን በአንድ ቃል ግለጽልን ያልነው ወጣት ወንድማገኝ ተሬሳ “ድሬ ማይክሮ ፋይናንስ ከፋይናንስ ተቋም በላይ ነው” በማለት ገልጾታል፡፡


Leave a Reply