ድሬ ማይክሮ ፋይናንስ በ2016 በጀት ዓመት ከ100 ሚሊየን ብር በላይ ማትረፉን ገለፀ

ድሬ ማይክሮ ፋይናንስ 2016 በጀት ዓመት100 ሚሊየን ብር በላይ ማትረፉን ገለፀ።

ጠቅላላ ሀብቱም ከ1.3 ቢሊየን ብር በላይ መድረሱን አስታውቋል።

ተቋሙ የ2016 በጀት ዓመት የቅርንጫፍና የዋናውን ቢሮ ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ አካሂዷል።

የተቋሙ የ2016 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም በቀረበበት ወቅት በ2016 በጀት ዓመት ለ3,755 የብድር ደንበኞች ብድር ለማሰራጨት አቅዶ የነበረው ተቋሙ ለ3,115 ደንበኞች ብድር ማሰራጨቱን ገልጿል፤ ይህም ከዕቅዱ አንፃር 83 በመቶ እንደሆነ የድሬ ማይክሮ ፋይናንስ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ተሾመ አበበ ተናግረዋል።

አቶ ተሾመ አክለውም ድሬ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም በ2016 በጀት ዓመት ከአንድ መቶ ሚሊየን ብር በላይ ማትረፉን እና ያልተጣራ ጠቅላላ ሀብቱም ከ1.3 ቢሊየን ብር በላይ መድረሱን ተናግረዋል።

ድሬ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም ራሱን በማዘመን በ2016 በጀት ዓመት የዲጂታል ብድርና የዲጂታል ቁጠባን  አገልግሎት የሚጠቀም ብቸኛው የሀገሪቱ ማይክሮ ፋይናስ ነው ሲሉም የተቋሙ ዋና ስራ አስፈፃሚው ተናግረዋል።

ከዚህ ቀደም በተቋሙ አደጋ ላይ ያለው የብድር መጠን 22 በመቶ የነበረ ሲሆን ፣ በዚህ በጀት ዓመት ላይ ግን ወደ አንድ በመቶ ዝቅ ማድረግ መቻሉም በሪፖርቱ ተመላክቷል።

በተጠናቀቀው በጀት ዓመት አስፈላጊውን ብድር በማመቻቸት ወጣቶች እና ሴቶች በስራ ላይ ተሰማርተው በአገር ዕድገት ላይ ተሳትፎ እና ተጠቃሚነታቸውን እንዲያሳድጉ  የተከናወኑ ስራዎች አበረታች ውጤት ማምጣታቸውንም የድሬ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም ዋና ስራ አስፈፃሚው አቶ ተሾመ አበበ ተናግረዋል፤

የተቋሙ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ተሾመ እንደገለፁት፤ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት  በአነስተኛ እና ጥቃቅን ስራዎች ለተደራጁ ኢንተርፕራይዞች አስፈላጊውን ብድር በማቅረብ የተሻለ ውጤት እንዲያመጡ በትኩረት ተሰርቷል። በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ለ2 ሺ 505 ኢንተርፕራይዞች ከ536 ሚሊዮን ብር በላይ በማበደር ወጣቶቹ በአገር የልማት ሥራዎች ላይ ተሳትፎና ተጠቃሚነታቸው እንዲጨምር ተደርጓል።

በተለይ በተለያዩ የስራ ፈጠራ ስራዎች ላይ የተሰማሩ 1 ሺ 7መቶ ሴቶች ከድህነትና ከጠባቂነት ለመውጣት የሚያከናውኗቸው ስራዎች ውጤታማ እንዲሆኑ ከ248 ሚሊዮን 345 ሺ ብር በላይ ብድር መሰራጨቱንም አቶ ተሾመ ተናግረዋል።

ከነዚህ በተጨማሪ መምህራን እና ሠራተኞች የዘመናት የቤት መስሪያ ቦታ ጥያቄ አስተዳደሩ  ምላሽ መስጠቱን ተከትሎ ባገኙት ቦታ የቤት ግንባታቸውን እንዲያፋጥኑ ተቋሙ በአነስተኛ ወለድ እና በረዥም ጊዜ ክፍያ የሚመልሱት 50 ሚሊዮን ብር በማበደር መሠረታዊ አስተዋጽኦ አበርክቷል ብለዋል።

የኮንዶሚኒየም ቤቶች ለደረሳቸው ነዋሪዎችም 60 ሚሊዮን ብር ብድር መሰራጨቱን በማስታወስ።

እንደተቋም በተከናወነው የተቀናጀ ስራ 253 ሚሊዮን 678 ሺ ብር ብድር በማስመለስ የዕቅዱን 98 በመቶ በመፈፀም ውጤታማ ስራ ተከናውኗል ብለዋል።በቁጠባም ረገድ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 702 ሚሊዮን ብር የሚጠጋ ቁጠባ መሰብሰቡን ጠቅሰዋል፡፡

ከመደበኛ ስራ ጎን ለጎን ከ4 መቶ ሺ ብር በላይ ወጪ በዝቅተኛ ኑሮ ውስጥ ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች ማዕድ ከማጋራት በተጨማሪ  በአረንጓዴ አሻራ እና በበጎ ፍቃድ የክረምት የልማት ስራዎች ላይ እየተሳተፉ መሆኑን ነው ዋና ሥራ አስፈፃሚው ያስረዱት።

ተቋሙ በዘንድሮ በጀት ዓመትም በዝቅተኛ ደረጃ የሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎችን ከድህነት ለማውጣት እና ሴቶችና ወጣቶች የጀመሯቸውን ውጤታማ የልማት ግስጋሴ ለማሳደግ በገጠርና በከተማ ዲጂታል የብድርና የቁጠባ አገልግሎቱን ተደራሽ በማድረግ የጀመራቸውን ውጤታማ ጥረቶች አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተመልክቷል።

In 2016 Fiscal Year, Dire Micro Finance Institution earned more than 100 million birr profit.

Its total assets reached more than 1.3 billion birr.

The institution held a forum for the execution of the summary plan of the branches and the main office for the 2016 fiscal year.

When the institution’s performance for the 2016 fiscal year was presented, the institution, which had planned to distribute loans to 3,755 loan customers in the 2016 fiscal year, stated that it distributed loans to 3,115 customers; this is 83 percent of the plan, said Teshome Abebe, CEO of Dire Microfinance.

Ato Teshome added that Dire Micro Finance Institution has made a profit of more than 100 million birr in the fiscal year 2016 and its total assets have reached more than 1.3 billion birr.

Dire Micro Finance Institution has updated itself in the 2016 fiscal year and is the only microfinance institution in the country to use digital loans and digital savings services, the CEO of the institution pointed out.

In the past, the portfolio at risk /PAR/ of the institution was 22 percent, but, now it has been reduced to one percent, according to the report.

 Teshome Abebe, Chief  Executive Officer of the Dire Micro Finance Institution, said that in the last financial year, the necessary loans were made available so that young people and women could engage in work and increase their participation in the country’s development and increase their benefits.

According to Mr. Teshome, the chief executive officer of the institution; in the last fiscal year, efforts were made to provide the necessary loans to small and micro enterprises so that they can achieve better results. By lending more than 536 million birr to enterprises with 2 thousand 505 members in the completed fiscal year, the participation and benefit of the youth in the country’s development activities has been increased.

Ato Teshome said that more than 248 million 345 thousand birr loans have been distributed so that the 1,700 women engaged in various entrepreneurship activities can be successful in their work to get out of poverty and poverty.

In addition to these, the institution has made a fundamental contribution by lending 50 million birr, which will be paid back with low interest over a long period of time, so that teachers and workers can speed up the construction of their houses in the places they have found, following the administration’s response to the demand for home work places. Remembering that 60 million birr loans have been distributed to the residents who have received condominium houses.

According to the Chief Executive Officer, the problem of  loan recovery that was threatening the existence of Dire  Microfinance Institution  has now been completely resolved through the coordinated work of the Dire dawa administration. He said that effective work has been done by recovering 253 million 678 thousand birr loans.   

In terms of savings, the CEO mentioned that nearly 702 million birr had been collected in the last fiscal year and announced that the institution.

According to Teshome Abebe, CEO of  Dire Micro Finance Institution, apart from regular work, they are participating in green legacy and voluntary summer development activities in addition to sharing food with the poor people at a cost of more than 400,000 Birr.

In this fiscal year, the institution will continue its effective efforts to lift the low-level society out of poverty and increase the effective development progress of women and youth by making digital credit and savings services accessible in rural and urban areas.

Dire Microfinance is currently an institution with more than 81,000 loan and savings customers.

    admin Avatar

    Leave a Reply

    Your email address will not be published. Required fields are marked *