ተምሳሌቶቹ

“ድሬ ማይክሮ ፋይናንስ ለእኔ የእናት ጓዳ ማለት ነው”

ሼፍ ካሳሁን እንዳሻው

የኤስ.ኬ.ሲ የምግብና መጠጥ ዝግጅት ማሰልጠኛ መሥራችና ባለቤት

ከእናት ጓዳ ምን ጠፍቶ ምን ታጥቶ ሁሉ ሙሉ ሁሉ ስንዱ ነው። እናት እጇን ዘርግታ የምትቀበል: ካላት የምታካፍል: ከማዕዷ የምታቋድስ ናት።

ሼፍ ካሳሁን እንዳሻውም ድሬ ማይክሮ ፋይናንስን በእናት ጓዳ የመሰለው ለእዚህ ነው። የራሱን ሥራ መጀመር ሲያስብ በሩን ከፍቶ በፍቅር ስላገለገለው ነው። ለሥራው የሚሆን ብድር ፈልጎ ወደ ተቋሙ ሲመጣ ብድር ተቋሙ ባቆመበት ጊዜ እንኳን የሥራ ዕንቅስቃሴውን የሥራ ቦታው ድረስ በመምጣትና በመመልከት እንደ እናት አለሁልህ ስላለው:ጓዳውን ከፍቶ ስላስተናገደው: የችግር ጊዜ ደራሹ ስለሆነ ነው።

ሼፍ ካሳሁን ውልደቱ ሂርና ሲሆን ዕድገቱ በድሬዳዋ ነው። በቴዎድሮስ ሆቴል ገና በማለዳው የሥራ ክቡርነት የገባው ሼፍ ካሳሁን ዕቃ በማጠብ: በመላላክ ለሥራ ያለውን ፍቅር አሳይቷል። ሥራ ክቡር ነው አይደለም ብሂሉስ።

በሠላም የምግብና የመጠጥ ዝግጅት ማሰልጠኛ ት/ቤት ለ4 ዓመታት ትምህርቱን የተከታተለው ሼፍ ካሳሁን በሲ.ኢ.ሲ.ሲ ሆቴል: በቢካፒታል ሆቴል: በአዳነ ሆቴል: በጅግጅጋ በኢስታንቡል ሆቴል:በሀዋሳና በባህር ዳርና በሀገረ ቻይና በምግብ ዝግጅት ባለሙያነት: በሆቴል ማማከርና ማደራጀት ሙያዊ አሻራውን አኑሯል።

ሼፍ ካሳሁን ከእነዚህ ሙያዊ አስተዋፆዎቹ በኋላ የራሱን ሥራ ለመጀመር ሲያስብ ከዓዕምሮው ሰሌዳ ላይ በጉልህ የሰፈረው ድሬ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም ነው። ብዙዎች ከተቋሙ ተበድረው ሲለወጡ አይቷልና እሱም ይህን ማድረግ እንዳለበት በመወሰን ወደ ድሬ ማይክሮ ፋይናንስ መስቀለኛ ቅርንጫፍ አመራ። በመጀመሪያም ባጃጅ መግዣ ብድር ወሰደና በአግባቡ በመሥራት ብድሩን ከፍሎ አጠናቀቀ። በሙያው ድሬዳዋ ላይ የሰለጠነ የምግብና የመጠጥ ዝግጅት ባለሙያ ክፍተት እንዳለ አስተውሎ ነበርና ቀጣይ የሥራ መዳረሻውን የምግብና መጠጥ ዝግጅት ማሰልጠኛ መክፈት ላይ አደረገ። ከዚያም ከድሬ ማይክሮ ፋይናንስ ተጨማሪ ብድር በመውሰድ ኤስ.ኬ.ሲ የምግብና የመጠጥ ዝግጅት ማሰልጠኛን ዕውን ማድረግ ቻለ።

ድሬ ማይክሮ ፋይናንስ ለትርፍ ብቻ የተቋቋመ ተቋም አይደለም እንደ እኔ ላሉ በርካታ ወጣቶች የሥራ ዕድል እንዲፈጥሩ ለሌሎችም እንዲተርፉ አይነተኛ ሚና መጫወቱን ሼፍ ካሳሁን ይገልፃል። ብድርን ለተፈለገው ዓላማ ማዋል ከተቻለ ማደግ:መለወጥ የሚያስችል ነውና ኅብረተሰቡ በተለይም ወጣቶች ተበድረው እንዲሰሩ: በአግባቡም ብድራቸውን እንዲከፍሉ አበረታታለሁ ይላል ሼፍ ካሳሁን።

እስከ አሁን ድረስ 580 ተማሪዎችን አስመርቆ 210 ሰልጣኞችን የሥራ ዕድል እንዲያገኙ ያደረገው ሼፍ ካሳሁን በዚህ ሁሉ ሂደት ውስጥ የድሬ ማይክሮ ፋይናንስ ዕገዛ በብዙ እንደጠቀመው ይናገራል።

ሙሉ የድግስ ዕቃ ኪራይ: የምግብና መጠጥ ዝግጅት ባለሙያዎችን ማሰልጠን: የሰለጠኑ ባለሙያዎችን ለሆቴል ማቅረብና ሆቴሎችን የማማከርና የማደራጀት ሥራዎች ላይ የተሠማራውና የድሬ ማይክሮ ፋይናንስ መስቀለኛ ደንበኛው ወጣቱ ሼፍ ካሳሁን ድሬ ማይክሮ ፋይናንስ በመስቀለኛ ቅርንጫፍ በሊዝ ፋይናንሲንግ የገዛለት ማሽኖች ለሥራው መሠረት ሆኖታል።

በድሬዳዋ ባለ 5 ኮከብ ሆቴል ለመክፈት የሚያልመው ሼፍ ካሳሁን ከሁለት ወራት በኋላ በሚከፍተው ኮምፖ ሬስቶራንት የሚያሰለጥናቸውን ተማሪዎች በሬስቶራንቱ ተጨማሪ የሥራ ዕድል ለሰልጣኞቹ ለመፍጠር ትጋቱን አጠናክሮ ቀጥሏል።

በዚህ ሁሉ የሥራ እንቅስቃሴው እንደ እናት ጓዳ በሩን ከፍቶ በፍቅር ያገለገለውን:ጓዳውን የከፈተለትን:ለዕድገቱ ለለውጡ የማዕዘን ድንጋይ የሆነለትን ድሬ ማይክሮ ፋይናንስን በልቡ አኑሯል።

ድሬ ማይክሮ ፋይናንስ ሥራው እንዲሠምርለት ቀኝ እጁ : ከትላንት እስከ ዛሬ አብሮት የተጓዘ ነገም አብሮት ያለ ተቋም መሆኑን በልበሙሉነት ይናገራል።

ድራ ማይክሮ ፋይናንስ በፍቅር አገልጋይ የእናት ጎዳ ነውና!

admin Avatar

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *