የድሬ ማይክሮ ፋይናንስ የዳይሬክተሮች ቦርድ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ በመወያየት ውሳኔዎች አሳለፈ
የተቋሙ የ2018 የሂሳብ ዓመት የስራ አፈጻጸም ሪፖርትና የቀጣይ ዓመት ዕቅድ በተቋሙ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ተሾመ አበበ የቀረበ ሲሆን በቀረቡ ሌሎች አጀንዳዎች ላይም በመወያየት ቦርዱ ውሳኔዎች አሳልፏል።
የድሬ ማይክሮ ፋይናንስ የዳይሬክተሮች ቦርድ ባደረገው ስብሰባ የተቋሙን የ2018 የሂሳብ ዓመት የስራ አፈጻጸም እና የ2019 የሂሳብ ዓመት ዕቅድ ከሰማ በኋላ የስራ አፈጻጸም ሪፖርቱንና ዕቅዱን በመገምገምና ሰፊ ውይይት በማድረግ አፅድቋል።
በክቡር ከንቲባ ከድር ጁኸር የቦርድ ሰብሳቢነት የተመራው የዳይሬክተሮች ቦርድ ድሬ ማይክሮ ፋይናንስ ከሌሎች ማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት ጋር የኮር ባንኪንግ ሲስተምን በጋራ /ሼርድ/ እየተጠቀመ እንደሚሰራና ይህም ተቋሙ በሚፈልገው መልኩና በእራሱ አሰራር ተንቀሳቅሶ እንዳይሰራ በተለይም የተቋሙን ዲጂታል የፋይናንስ አገልግሎት አሰጣጥን ከማዘመን አንጻር የኮር ባንኪንግ ግዢ እንዲደረግለት የቀረበው አጀንዳ ላይ ተወያይቶ ግዥው እንዲፈጸም ውሳኔ አሳልፏል። ቦርዱ ባደረገው ስብሰባ የተቋሙን የውጭ ኦዲተርም ሰይሟል።
የድሬ ማይክሮ ፋይናንስ የስራ አመራር ቦርድ ተቋሙ ለብድር የሚሆን ሀብት በመሰብሰብ ረገድ እያደረገው ላለው ጥረት አድናቆቱን የሰጠ ሲሆን በቀጣይ የኅብረተሰቡን የፋይናንስ ተጠቃሚነት ከማሳደግ አንጻር የቁጠባ አሰባሰብ ስራዎችን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ አቅጣጫ አስቀምጧል።
የድሬ ማይክሮ ፋይናንስ የዳይሬክተሮች ቦርድ ለተቋሙ እያደረገ ያለው ድጋፍና ክትትል ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተገልጿል።














Leave a Reply