የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባና የድሬ ማይክሮ ፋይናንስ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ አብዱላሂ አደን ከተቋሙ የቦርድና የማኔጅመንት አባላት ጋር የትውውቅ መድረክ አካሂደዋል።
በመድረኩ የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ተሾመ አበበ የድሬ ማይክሮ ፋይናንስን ታሪካዊ ዳራ፣ የፋይናንስ አፈጻጸም፣ አሁናዊ ሁኔታ፣ የወደፊት የሥራ አቅጣጫዎችና ትኩረት የሚሹ ጉዳዮችን በተመለከተ ሰፊ ገለጻ አቅርበዋል።
በገለጻቸውም ተቋሙ በተለያዩ የፋይናንስ መለኪያዎች ቀጣይነት ያለው ዕድገት እያሳየ መምጣቱን ጠቁመዋል። በዚህም በደንበኞች እጅ ያለው የብድር መጠን ከ1.8 ቢሊዮን ብር በላይ መድረሱን እና የአደጋ ስጋት ያለበት የብድር ምጣኔ (Portfolio at Risk – PAR) እስከ 0.65 በመቶ መውረዱን አብራርተዋል።
የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ እና የድሬ ማይክሮ ፋይናንስ ቦርድ ሰብሳቢ ክቡር አቶ አብዱላሂ አደን የወጣቶች ተዘዋዋሪ ብድር በተሳካ ሁኔታ እንዲመለስ እና ተቋሙ የራሱ የሆነ ሕንፃ እንዲኖረው በቀጣይ ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሠራ ገልጸዋል። በተጨማሪም የድሬዳዋ አስተዳደር ለተቋሙ የሚያደርገው ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።
የትውውቅ መድረኩ በተቋሙ የሥራ አፈጻጸም፣ በወደፊት የዕድገት አቅጣጫዎችና በተቋማዊ አቅም ግንባታ ዙሪያ ያለውን ትብብር ለማጠናከር አስፈላጊ መሠረት በመጣል ተጠናቋል።






Leave a Reply