የደንበኞችኮንፈረንስናየዕውቅናመድረክተካሄደ

ድሬ ማይክሮ ፋይናንስ የመስራት አቅም እያላቸው በአቅም ውስንነት ወደ ግባቸው መድረስ ላልቻሉ የህብረተሰቡ ክፍሎች ወደ ግባቸው እንዲደርሱ እገዛ እያደረገ ያለ ተቋም ነው

ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር

ድሬ ማይክሮ ፋይናንስ የውጤታማ ደንበኞች ኮንፈረንስና የዕውቅና መድረክ   አካሂዷል።

በመርሃ ግብሩም ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ እና የድሬ ማይክሮ ፋይናንስ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ከድር ጁሃር ድሬ ማይክሮ ፋይናንስ ለህብረተሰቡ እየሰጠ ያለው አገልግሎት ላቅ ያለ መሆኑን ጠቅሰው ተቋሙ በቀጣይ የሚሰጠውን አገልግሎት ይበልጥ ተደራሽ እንዲሆን ለማስቻል አስተዳደሩ አስፈላጊውን እገዛ እንደሚያደርግ ተናግረዋል።

ድሬ ማክሮ ፋይናንስ በመደበኛው የባንክ አገልግሎት ተጠቃሚ መሆን ላልቻሉ የኅብረተሰብ ክፍሎች የፋይናንስ ተጠቃሚነታቸውን ያረጋገጠ የፋይናንስ ተቋም መሆኑን በተግባር የገለጠ ጭምር እንደሆነ የጠቆሙት ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር በመደበኛ ብድር የማግኘት ዕድል ያልነበራቸው ወጣቶች እና ሴቶች አሁን በተቋሙ አማካኝነት ተጠቃሚ መሆን መቻላቸውን ጨምረው ተናግረዋል።

የድሬ ማይክሮ ፋይናንስ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ተሾመ አበበ በበኩላቸው ተቋሙ በመደበኛው የባንክ አገልግሎት ተጠቃሚ መሆን ላልቻሉ የኅብረተሰብ ክፍሎች የፋይናንስ ተጠቃሚነታቸውን ያረጋገጠ እና አጋርነቱን በተግባር የገለጸ ተቋም መሆኑን ተናግረዋል።

ድሬ ማይክሮ ፋይናንስ አገልግሎቱን ዘመናዊ እና ቀልጣፋ ለማድረግ አዳዲስ አሰራሮችን እና ዘመኑን የዋጁ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ላይ እንደሚገኝ የገለጹት አቶ ተሾመ በቀጣይም አገልግሎቱን ለማስፋት በአዲስ አበባ እና ሀሮማያ አዳዲስ ቅርንጫፎችን በመክፈት ወደ ህብረተሰቡ ይበልጥ ለመቅረብ እየሰራ መሆኑን ገልፀዋል።

የድሬ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም የውጤታማ ደንበኞች ኮንፈረንስና የዕውቅና መድረክ ላይ በብድር እና ቁጠባ ሞዴል የሆኑ ደንበኞች እና ግንባር ቀደሞች እንዲሁም ባለድርሻ አካላት ከዕለቱ የክብር እንግዶች እጅ የተዘጋጀውን ሰርተፍኬት እና ክርስቲያል ዋንጫ ተቀብለዋል።

admin Avatar

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *